የኛ ስቶክ (Yegna Stock) በኢትዮጵያ ለሚገኙ የችርቻሮ፣ የጅምላ ነጋዴዎች፣ ሱፐርማርኬቶች፣ ፋርማሲዎች እና የመጋዘን ባለቤቶች የተሰራ ዘመናዊና ሙሉ የሽያጭ እና የመጋዘን መቆጣጠሪያ (Cloud POS & Inventory Ecosystem) ሶፍትዌር ነው። በየኛ ቴክ ሶሉውሽን (Yegna Tec Solutions) የበለፀገው ሲስተማችን፣ ንግድዎን ከወረቀትና ከኤክሴል አሰራር ውዝግብ በማውጣት ሙሉ በሙሉ በዲጂታል አውቶሜሽን እንዲመሩ ያስችላል።
በማንኛውም ቦታና ጊዜ ሆነው የዕቃዎችን ክምችት፣ የመጋዘን ዝውውርን፣ የሰራተኞችን እንቅስቃሴ፣ የባርኮድ ሽያጭን እና እለታዊ የትርፍና ኪሳራ ሂሳቦችን በሪል-ታይም መከታተል ይችላሉ። በተጨማሪም በቴሌግራም አውቶሜሽን እና ከኢንተርኔት ውጭ (Offline) መስራት በሚያስችለው ቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ የመጋዘን ስርቆትንና የገንዘብ ኪሳራን በቋሚነት ያስወግዳል!
በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ንግዶች የፋይናንስ፣ የክምችት፣ የሰው ኃይል፣ የስትራቴጂ እና የኦፕሬሽን ተዳጋጋሚ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። የኛ ስቶክ (Yegna Stock) እነዚህን ሁሉ ተዳጋጋሚ ስጋቶች በዘመናዊ አውቶሜሽን፣ በ AI እና በPWA Offline-First ቴክኖሎጂ በዘላቂነትና በአስተማማኝነት ለመፍታት የተገነባ አጠቃላይ የኢንቬንተሪና POS ሲስተም ነው።
የኛ ስቶክ የገቢዎችንና የወጪዎችን ታክስ (VAT/TOT) እና የ Withholding Tax (2% / 30%) ሂሳብ በራስ-ሰር ያሰላል። ከሲስተሙ በቀጥታ ለገቢዎች ሚኒስቴር እና ለኦዲት የሚሆኑ የፋይናንስ ሪፖርቶችን በ 1-Click ማውጣት ይቻላል። የኦዲት ስህተቶችንና የቅጣት ስጋቶችን ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል!
ሲስተሙ ዋና ካፒታልን፣ የቃ ግዥ ወጪን እና የተጣራ ትርፍን (Net Profit) ለይቶ ያሳያል። የካሽ ዝውውር ለግል ፍጆታ ውሎ ካፒታል እንዳይቀንስ ይከላከላል።
የኪራይ፣ ደሞዝ፣ መብራት/ውሃ እና አነስተኛ ወጪዎችን በየምድቡ የመመዝገቢያ ዳሽቦርድ ስላለው የንግዱን እውነተኛ አትራፊነት ያሳያል።
የደንበኞችና የሰፕላየሮች የብድር መዝገብ (Credit Ledger) ከነተከፋይ ቀን ማስታወሻና አውቶማቲክ ኤስኤምኤስ/ቴሌግራም ማስታወሻ ጋር ይዟል።
አዲስ እቃ በውድ ሲገባ የነባሩን እቃ የመሸጫ ዋጋ በራስ-ሰር ማስተካከያ (Batch Pricing & Dynamic Margin) በማስላት የመተኪያ ካፒታልን ይጠብቃል።
ለፋርማሲ፣ ኮስሞቲክስና ሱፐርማርኬት የመጠቀሚያ ቀናቸው ከመድረሱ ወራት በፊት አውቶማቲክ ማስጠንቀቂያ ይልካል። FEFO (First-Expired, First-Out) አሰራርን ይተግብራል።
የማይሸጡና ካፒታል ያሰሩ እቃዎችን በ AI አናሊቲክስ ለይቶ በማሳወቅ በዲስካውንት ወይም በማስተዋወቅ እንዲወጡ ምክረ-ሐሳብ ይሰጣል።
እያንዳንዱ እቃ ከተቀመጠለት ዝቅተኛ መጠን (Re-order Threshold) በታች ሲወርድ አውቶማቲክ መልዕክት በመላክ ደንበኛ እንዳያመልጥ ያደርጋል።
እያንዳንዱ እቃ በመጋዘንና በሱቅ መካከል ሲንቀሳቀስ፣ ሲሸጥ ወይም ሲሰረዝ በባርኮድ እና በባለታሪክ መዝገብ (Audit Log) ስለሚመዘገብ ስርቆትን 100% ያስቀራል።
በሺዎች የሚቆጠሩ እቃዎችን በ Category፣ Sub-category እና SKU Variants (ቀለም፣ መጠን፣ ብራንድ) ከፍሎ በሴኮንዶች ውስጥ በቀላሉ ለመፈለግ ያስችላል።
ባለቤቱ በሌለበት ሰራተኞች በገደብ (Role permissions) እንዲሰሩ ያደርጋል። ባለቤቱ በስልኩ ወይም በቴሌግራም ቦት የትም ሆኖ ስራውን ይቆጣጠራል።
እያንዳንዱ ሻጭ በራሱ አካውንት ገብቶ ስለሚሸጥ፣ የካሽ መዛባት ቢፈጠር በግልጽ እንዲታወቅ በማድረግ ፍጹም ግልፅነትን ይፈጥራል።
ሲስተሙ ለመማር በጣም ቀላልና ግልፅ በመሆኑ አዲስ ሰራተኛ ቢቀጠር በ 10 ደቂቃ ውስጥ ስልጠና ወስዶ መስራት እንዲጀምር ያስችላል።
ፈጣን የ POS ረሲት ማተሚያ፣ የደንበኞች የግዢ ታሪክ (Loyalty) እና አውቶማቲክ ቅናሽ አሰራር ስለለው ደንበኞችን ያረካል።
በየቀኑ፣ በየሳምንቱ እና በየወሩ ከፍተኛ ተፈላጊ የሆኑ እቃዎችን፣ አትራፊ ደንበኞችንና የሽያጭ ገበታዎችን በምስል (Charts) ያቀርባል።
የዲጂታል ክፍያዎች (ቴሌብር፣ CBE Birr፣ ባንክ ትራንስፈር) እና የQR-Code/Barcode አሰራርን በማካተት ንግድዎን ዘመናዊ ያደርጋል።
አንድ ቦታ ሆነው በብዙ ከተሞች ወይም ቦታዎች ያሉ ቅርንጫፎችና መጋዘኖችን የክምችት ዝውውርና የሽያጭ ሁኔታ በአንድ ማዕከላዊ ዳሽቦርድ ይቆጣጠራሉ።
የደንበኞችን የግዢ ፍላጎትና ተደጋጋሚ ግዢዎችን በመተንተን ትክክለኛውን ምርት ለትክክለኛው ደንበኛ ለማቅረብ የሚያስችል ዳታ ይሰጣል።
በማናቸውም ስልክ፣ ታብሌት ወይም ላፕቶፕ ላይ ያለ ተጨማሪ ውድ ሃርድዌር ይሰራል፤ መጫንም (Installation) አይጠይቅም።
በደብተርና በካልኩሌተር መስራትን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል። የሂሳብ ስህተቶችን በ 0% አውቶሜሽን ደረጃ ያወርዳል።
እያንዳንዱ እቃ የተቀመጠበትን የመጋዘን የመደርደሪያ ቁጥር (Shelf/Aisle Location) በሲስተሙ በመመዝገብ እቃ የመፈለግ ጊዜን ይቆጥባል።
ተሳስቶ የተሸጠ ወይም የተመዘገበ ሂሳብ ሲኖር ፈቃድ ባለው አካል በ 1-Click የስህተት ማስተካከያ (Void/Return Log) መስራት ያስችላል።
የኛ ስቶክን በመጠቀም የንግድዎ ባለቤትና ሙሉ ተቆጣጣሪ ይሁኑ። የታክስና ዊዝሆልዲንግ ሪፖርቶችን ጨምሮ ሁሉንም የንግድ ስጋቶች በአንድ ሲስተም ይፍቱ።
አሁኑኑ ያግኙን / ይጀምሩ