ንግድዎን ከዕለታዊ አድካሚ የወረቀት ስራ ወደ ሙሉ ዲጂታል አውቶሜሽን የሚያሸጋግሩ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች።
የዕቃዎችን ብዛት፣ የመጠቀሚያ ጊዜ (Expiry Date)፣ እና የተቀመጡበትን ቦታ (Shelf/Aisle) በሪል-ታይም መከታተል። እቃ ከዝቅተኛ መጠን በታች ሲወርድ አውቶማቲክ ማስጠንቀቂያ ይልካል።
በፈጣን የሽያጭ መመዝገቢያ። የደረሰኝ ማተሚያ (Receipt Printing) ክፍያዎችን በመመዝገብ በአንድ ላይ ያቀላጥፋል።
በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ቅርንጫፎችንና መጋዘኖችን በአንድ ማዕከላዊ ዳሽቦርድ መቆጣጠር። በቅርንጫፎች መካከል የሚደረግን የዕቃ ዝውውር (Stock Transfer) በግልጽ መከታተል።
የ VAT/TOT እና የ Withholding Tax አውቶማቲክ ስሌት። ለኦዲት እና ለገቢዎች ሚኒስቴር የሚሆኑ ሪፖርቶችን በ 1-Click ማውጣት ይቻላል።
የባለቤቱን ስልክ በቀጥታ ከሲስተሙ ጋር በማገናኘት የእለታዊ ሽያጭ፣ የካሽ መጠን እና የስቶክ እንቅስቃሴ ሪፖርቶችን በቴሌግራም መልዕክት ማግኘት።
ኢንተርኔት ቢቋረጥ እንኳ ስራዎን አያቆሙም። PWA Offline ቴክኖሎጂ ሽያጮችን መዝግቦ ኢንተርኔት ሲመጣ አውቶማቲክ ከክላውድ ጋር ያመሳስላል (Sync)።